በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
“ተሰጥመ ሞት ውስተ መአት፤ ሞት ድል በመነሣት ተዋጠ” ፩ ቆሮ ፲፭፡፶፬
ከሲኦል እጅ ሊታደገን የመጣው ንጉሥ ከሞት ተነስቶልናል፤ ለዘመናት ሠልጥኖብን የኖረው ሞት ከክርስቶስ በኋላ የእርሱን ስም ሰምቶ መደንገጥ እና መንቀጥቀጥ ግብሩ ሆኗል።
የሚያስጨንቀን የነበረው የመቃብር ድንጋይ ከሕይወታችን መንገድ ተወግዷል፤ የምንሻውን የናዝሬቱን ኢየሱስንም አግኝተነዋል የሞትን ኃይል ሲያመሰስነውም ተመልክተናል።
የትንሣኤውን ክብር ይገልጥ ዘንድም ጥቂት ብርሃንን አውጥቶ የመቃብር ጠባቂዎችን ሲጥላቸው ያየነው እርሱ በመለኮታዊ ብርሃኑ ጨለማን አስወግዶ በብርሃን መርቶናል።
በአዳም ያጣነውን ልጅነት በክርስቶስ ኢየሱስ አግኝተነዋል ፤ ከመሪቅት ብርሃኑ ተጎናጽፈናል፤ ከስደት ወደ አባታችን ቤት ተመልሰናል፤ ከረሃብና ከጠማት በሥጋውና በደሙ ጠግበናል፤ ከዲያብሎስ ተገዥነት ወደ ልባችን ደስታ ተጠግተናል፤ ውርደታችን በጌታ ትንሣኤ በክብር ተለውጧል።
ስለዚህ በሞት ተጀምሮ በትንሣኤው የተረጋገጠልን የሕይወታችን ነገር እንዲህ ከሆነ ያከበረንን አምላክ ደስ እናሰኘው ዘንድ ምክንያት አለን፤ ምን ጊዜም በበጎ ነገር እንጽና፤ የተቸገሩ ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን እናስባቸው፤ ለሰውና ለፍጥረት ሁሉ መልካሙን እናድርግ፤ የተከፈለልንን ዋጋ መመለስ እንደማይቻልን ተረድተን የትንሣኤውን ብርሃን ያሳየንን ድንቅ አምላክ እናመስግነው በመልካም ሥራም እንጽና !
እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ !
Administration & Contact
- Administrator: Melake Selam Aba G/Michael G/Kidane (Komoss), The Church Administrator
- Amharic Title: መልአከ ሰላም አባ ገ/ሚካኤል ገ/ኪዳን (ቆሞስ) የደብሩ ዋና አስተዳዳሪ
- Scripture Quote: “Michael, one of the chief princes, came to help me – Daniel 10:13”
- Amharic Quote: ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ – ዳን 10፡13
- Website: www.stmichaeleotc.com
- Email: info@stmichaeleotc.com
- Phone: +1 (510) 230-3071
- Social Media: @St.MichaelEOTC
