Debre Selam St. Michael and St. Mary Ethiopian Orthodox Tewahedo Church - Sacramento, California

ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ወቅድስት ድንግል ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን - ሳክራሜንቶ ካሊፎርኒያ

እሱ ግን ከተናገረው አንዱንም ሳያስቀር ተነሳሣ!

“ይህን ቤተመቅደስ አፍርሱት በሦስተኛው ቀን አነሣዋለሁ” ዮሐ. 2፥19 አላለም ነበር?
እንደተናገረ ቤተ መቅደስ የተባለ ሰውነቱን አስነሥቶ አሳየን።

“እኔ በፈቃዴ አኖራታለሁ እንጂ ነፍሴን ከእኔ ማንም አይወስዳትም ላኖራት ሥልጣን አለኝ ደግሞም ላነሣት ስልጣንአለኝ” ዮሐ. 10፥18 ያለውን ቃሉን ሊፈጽም ጌታ ተነሣ።

በዚያ ቦታ ተገኝተው መቃብሩ ባዶ ሆኖ ያዩት ሴቶች እንዴት የታደሉ ናቸው?

“መልአኩ አይዟችሁ አትፍሩ” ብሎ አጽናናቸው፤ መቃብሩ ባዶ ሆኖ ከማየት በላይ የሚያጽናና ነገር አለ?

እስኪ ንገሩኝ “እንደ ተናገረ ተነሥቷል በዚህ የለም ከሙታን ጋር ስለምን ትፈልጉታላችሁ?”

የሚለውን የሚመስል የሚያረጋጋ ቃል ከየት ይገኛል?

መዋዔ ሞት መዋዔ ኃጢአት ጌታ ተነሥቷል

እንኳን ደስአላችሁ
እንኳን አደረሳችሁ!

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *